*Announcement* Anbesa Bank has officially rebranded It's Identity.

(ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም) በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲደረግ የነበረው የ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሶስተኛው ሩብ ዓመት እና የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡

ለሁለት ቀናት በቆየው ይህ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ የባንካችን ፕሬዝደንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ባንኩ በሐብት አሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ በዲጅታል ባንክ አገልግሎት (ተደራሽነት) እና በመሳሰሉት፤ በመገምገም የተመዘገቡ ውጤቶች እንዲቀጥሉ እና እንዲጠናከሩ አሳስበዋል፡፡ መሻሻል በሚገባቸው አፈጻጸሞች ላይ ተገቢውን ማስተካከያ በማድረግ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ አስፈላጊ መሆኑን በአፅንዖት ገልፀዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች፣ የሪጅናል ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የዲስትሪክት ኃላፊዎች ተሳትፎ በማድረግ ውይይት አድርገዋል፡፡

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

Leave A Comment