*Announcement* Anbesa Bank has officially rebranded It's Identity.

ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ.ም) አንበሳ ባንክ እ.ኤ.አ. የ2025/26 በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ አመት እና የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ስብሰባ በዋና መስሪያ ቤት መስብሰቢያ አዳራሽ በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል፡፡

የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ስብሰባውን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት የከፈቱ ሲሆን መልዕክቱን ተከትሎ የባንኩ የሶስተኛ ሩብ ዓመት እና የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል፡፡ በሪፖርቱ ዙሪያ በስብሰባው ላይ የተገኙ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራሮች፣ የሪጅናል ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የዲስትሪክት ኃላፊዎች ውይይት አድርገዋል፡፡

ጉባዔው የተለያዩ የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በማዳመጥ እና ውይይቶችን በማድረግ እስከ ነገ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል::

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

Leave A Comment