News

በአዲስ አበባ ሪጅን የሚገኙ ዲስትሪክቶች አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ሲንየር ኤክዘክዩቲቭ ማኔጅመንት በአዲስ አበባ ሪጅን ስር ከሚገኙ ዲስትሪክቶች ጋር በ2016 የመጀሪያ ሩብ የበጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡
ትናንት መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው ግምገማ በአዲስ አበባ ሪጅን ስር የሚገኙ አምስት ዲስትሪክቶች የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፈጻጸም ላይ በታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡
በሩብ የበጀት ዓመቱ የታዩ ድክመቶችን በማረምና የነበሩንን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ በማጠናከር አሁን የተመዘገበውን አበረታች ውጤት አጎልብቶ ለማስቀጠል የሚያስችል አቅጣጫ ከማኔጅመንት እና ከቦርድ የተሰጠ ሲሆን፤ በሁለተኛ ሩብ የበጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ማኔጅመንት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁሉም ሠራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ፕሮግራም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አስፋው ለሁሉም የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች የሰላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆንላቸው በመመኘት በአዲሱ ዓመት ባንኩን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩበት ጊዜ እንደሚሆን ገልፀዋል። ባንኩ ከምንጊዜውም ይበልጥ በርካታ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየሰራ በመሆኑ አሁን ላይ ህብረተሰቡ ለባንኩ ያለው አመለካከት ከሚጠበቀው በላይ አበረታች ስለሆነ ይህን ተስፋ ሰንቀን ረጅም ርቀት መጓዝ እንችላለን ብለዋል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ በበኩላቸው አዲሱ ዓመት ለተጨማሪ ስኬት የሚያበቁን መሠረቶች ጥለን ለውጤት የምንበቃበት እንደሚሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ማኔጅመንቱና ሰራተኛው በአዲሱ አመት አዲስ ተስፋ ሰንቀው በሁሉም ዘርፍ ጠንክረው በመስራት በበጀት አመቱ የያዝናቸውን አቅዶች በማሳካት ውጤታማነታችንን የምናረጋግጥበት አመት ይሆል ብለዋል።

የዘንድሮው አዲስ አመት ካለፉት ለየት የሚያደርገው ባንኩ አስፀድቆ ወደ ትግበራ ያስገባውን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ተፈፃሚ ለማድረግ አንድ ብሎ የጀመረበት በመሆኑ የባንኩ አመራር እና ሠራተኞች እቅዱን ለማሳካት ከመቼውም በላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ለሁሉም የባንኩ አመራሮች እና ባለ ድርሻ አካላት እንዲሁም ደንበኞች መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልፀዋል።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የትግራይ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ አለም አስፋው በተገኙበት በባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና በትግራይ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ተኸላይ አበበ መካከል ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የስብሰባ አዳራሽ የተፈረመው ስምምነት ሁለቱም ተቋማት የጋራ በሆኑ ስራዎች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡

በስምምነቱ መሰረት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ኢንስቲትዩቱ በግብርና ምርምር ዘርፍ በሚያከናውናቸው ስራዎች ሁሉ አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅርቦት የሚሰጥ ሲሆን፤ ኢንስቶትዩቱም ለምርምር ስራው ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚያገኘውን ፋይናንስ አቅርቦት በአንበሳ ባንክ በኩል ያንቀሳቅሳል፡፡ የትግራይ ምርምር ግብርና ኢንስቲትዩት በገጠሩ ማሕበረሰብ ውስጥ ዘልቆ የሚሰራ እንደመሆኑ አንበሳ ባንክ በክልሉ ያለውን የቅርንጫፎች ቁጥርና ተደራሽነት ተቋሙ የባንክ አገልግሎትን በቅርበትና በቅልጥፍና ለማግኘት የሚያስችለው በመሆኑ አንበሳ ባንክ ተመራጭ ባንክ እንደሚያደርገው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

ለስምምነቱ መሳካት ሁለቱም ወገኖች በትጋት እንደሚሰሩም ተገልጿል፡፡

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በባንኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ በመቐለ ከተማ ከሚገኙ ባለአክስዮኖች ጋር ምክክር አካሄደ።

ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በአክሱም ሆቴል በተካሄደ የምክክር መድረክ በባንኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ የ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም፣ የቀጣይ አቅዶች እንዲሁም የባንኩን የተከፈለ ካፒታል ማሳደግ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ባለፈው ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለአክስዮኖች ጋር ተመሳሳይ ውይይት ማካሄዱ ይታወቃል።

በተጨማሪም ባንኩ ያዘጋጀው አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፤ ባንኩን ወደ ተሻለ ከፍታ እንደሚወስደው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር!

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሐጎስ ዛሬ ነሐሴ 11 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተፈረመው ስምምነት ሁለቱም ተቋማት በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በዚህም መሰረት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዩኒቨርሲቲው ለሚያካሂዳቸው ስራዎች አስፈላጊውን የፋይናንሻል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፤ መቐለ ዩኒቨርሲቲም የባንኩን የሰው ኃይል አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችንና የቴክኒካል ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ባንኩ ዩኒቨርሲቲው ለሚያስመርቃቸው ባለሙያዎች የስራ ዕድል በመፍጠር የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር !

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በባንኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙሪያ ከባለአክስዮኖች ጋር ምክክር አካሄደ።

ዛሬ ሐምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል በተካሄደ የምክክር መድረክ በባንኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ የ2015 ዓ.ም አፈፃፀም፣ የቀጣይ አቅዶች እንዲሁም የባንኩን የተከፈለ ካፒታል ማሳደግ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር!

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዲስ አበባና በክልሎች ከሚገኙ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የ2015 የበጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡

አንበሳ ባንክ ከቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች እና ከዋና መስሪያቤት ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎች ጋር ረቡዕ ሐምሌ 12 እና ሐሙስ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሳፋዬር ሆቴል ባካሄደው ግምገማ ባንኩ በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙት ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጦባቸዋል፡፡ ባንኩ በ2014/15 የበጀት ዓመት ያሳየው አፈጻጸም የተሻለ አንደነበርና ውጤቱም በሰራተኞችና ደንበኞች ላይ መነቃቃት የፈጠረ መሆኑን ተመልክቷል፡፡ በበጀት ዓመቱ የደንበኞች ፍላጎትን ያገናዘቡ አዳዲስ አገልግሎቶች ወደ ገበያ ማቅረቡም ለአዲሱ የበጀት ዓመት አፈጻጸም ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖሮው ተገልጿል፡፡ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት መልካም አፈጻጸም ላስመዘገቡ 20 ቅርንጫፎችም የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ባንኩ በተጨማሪም ለቀጣይ አምስት አመታት ያዘጋጀውን አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ በቅርንጫፍ ስራአስኪያጆች እና በዋና መስሪያ ቤት የስራ ኃላፊዎች ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ ሰትራቴክ ዕቅዱ ባንኩን ወደ ተሻለ ከፍታ እንደሚወስደው ም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሰሜን ሪጅን ከሚገኙ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የ2015 የበጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ፡፡

ባንኩ በክልሉ የሚገኙ ቅርንጫፎች በበጀት ዓመቱ ዘግይተው ወደ ስራ ቢገቡም በነበሩት ቀሪ ወራት ባሳዩት አፈጻጸም፣ በቀጣይ ዓመት ዕቅድና በጀት እንዲሁም በአዲሱ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል፡፡
በበጀት አመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ቅርንጫፎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጥቷል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የስኬትዎ አጋር!

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ “Anbesa Fund” የተባለ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ፕላትፎርም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የማስተዋወቅያ መድረክ አካሄደ፡፡

ባንኩ በቅርቡ በይፋ ያስመረቀውን ‘Anbesa Fund’ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ፕላት ፎርም በሃገራችን በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሳቢያ የወደሙ ማህበራዊ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እና የህብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታት በትግራይ ክልል እየተንቀሳቀሱ ለሚገኙ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተጠቅመው ከዲያስፖራው ማህበረሰብ የዕርዳታ ገንዘብ ማሰባሰብ እንዲችሉ ሰሞኑን ባዘጋጀው መድረክ አስተዋውቋል፡፡ በክልሉ በትምህርት፣ በጤና፣ በንፁህ የመጠጥ ውሃ እና በሌሎች ፕሮጄክቶች መልሶ ግንባታ የተሰማሩ ድርጅቶችና የክልሉ ቢሮዎች በማስተዋወቅያ መድረኩ ከባንኩ የተሰጠውን መግለጫና ማብራሪያ የተከታተሉ ሲሆን፤ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ፕላት ፎርሙ ለስራቸው አጋዥ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ አንበሳ ፈንድ (Anbesa Fund) የእርዳታ ማሰባሰቢያ platform ድረ-ገፅን መሰረት አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ዲያስፖራዎች ስልኮቻቸውንና ሌሎች የትስስር ገፆቻቸውን በመጠቀም ወደ አንበሳ ፈንድ ድረ-ገፅ www.anbesafund.com በቀላሉ በመግባት የፈለጉትን ያህል የገንዘብ ልገሳ በማድረግ በሀገራቸው ልማት ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ለመሆን ያስችላቸዋል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከተጎጋ ስሚንቶ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር ጋር ዘላቂ የሆነ አጋርነት ለመመስረት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

ባንኩ እና በምሰረታ ላይ ያለው ተጎጋ ስሚንቶ ፋብሪካ ቅዳሜ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በመቐለ ደስታ ሆቴል የስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነቱን የተፈራረሙት አክስዮን ማህበሩ አጠቃላይ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በአንበሳ ባንክ ለማድረግ እና ባንኩ ደግሞ ለፋብሪካው ምስረታ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ለማቅረብ ነው።

በዚህም መሠረት የተጎጋ ስሚንቶ ማህበር ከአክስዮን ሽያጭ የሚያሰባስበውን ገንዘብ በባንኩ የሚያስቀምጥ ሲሆን፣ አባላቱም የገንዘብ እንቅስቃሴአቸውን ከአንበሳ ባንክ ጋር እንዲያደርጉ የማግባባት ስራ እንደሚሰራ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሸናፊ ሃይለ ገልፀዋል።

አንበሳ ባንክ በበኩሉ ፋብሪካው ከምስረታ ጀምሮ እስከ ተከላና ምርት መጀመር ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ የሚያስፈልገውን የፋይናንስ አቅርቦት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አቶ ዳንኤል ተከስተ የባንኩ ፕሬዝደንት ገልፀዋል።

ለፋብሪካው ግብዓት ከሚያስፈልገው የፋይናንስ አቅርቦት በተጨማሪ የፋበሪካውን አክስዮን በብዛት መግዛት ፈልገው በገንዘብ እጥረት ምክንያት መግዛት ላልቻሉ በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የአክስዮን ምስክር ወረቀቶቻቸውን በዋስትና በመያዝ ለተጨማሪ አክስዮን መግዣ የሚውል ብድር የሚሰጥ መሆኑን አስታውቀዋል። ከብድር አቅርቦቱ ተጨማሪ አክስዮን የመግዛት ፍላጎት ያላቸው የንግድ ማህበረሰብ አባላትም የሚያካትት መሆኑን ተገልጿል።
በተጨማሪም ባንኩ በቅርቡ ሰራ ላይ ባዋለው አንበሳ ፈንድ በተባለ ዲጂታል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕላትፎርም አማካይነት የፋብሪካውን አክስዮን ሽያጭ ለማቀላጠፍ እንደሚሰራ አቶ ዳንኤል አመልክተዋል።

አንበሳ ኢንተርናሽናል

Anbesa School Pay

Contact Us

Tel: (+251) 11 662 60 00/60
Fax: (+251) 11 662 59 99
P.O.Box: 27026/1000 Addis Ababa
E-mail: info@anbesabank.com
SWIFT Code: LIBSETAA
Address: Haile G.Selassie Avenue, Lex Plaza Building Addis Ababa, Ethiopia