የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች 22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር -ተቋምን በአሰራር!” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሕዳር 26 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አክብረዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ የሪቴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሚካኤል ገዛኢ እንደገለፁት ሙስና ዘርፈ ብዙ እና በተለያዩ ጊዜያቶች ይዘቱን ቀይሮ የሚመጣ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም የስራ ኃላፊዎች የዕለት ተዕለት ስራቸው መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ሙስናን ለመዋጋት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችም በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የሐብት ምዝገባ ቅፁን ሞልተው ለባንኩ የፀረ ሙስና ኮሚሽን መከታተያ ቢሮ በማስረከብ አረአያነታቸውን አሳይተዋል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር

Leave A Comment