በ18ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ መደበኛ ስራውን ጀመረ፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርዱ ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ስራውን የጀመረው አዲስ ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሊቀ-መንበር በመምረጥ ሲሆን፤ አቶ አለም አስፋውን ሊቀ-መንበር፤ ዶ/ር አክሊሉ ገ/ስላሴን ደግሞ ምክትል ሊቀ-መንበር አድርጎ መርጧል፡፡ ቦርዱ በተጨማሪም ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችሉት ሦስት ንኡሳን ኮሚቴዎችን አዋቅሯል፡፡
ቦርዱ የመጀመሪያ ስራውን ያደረገው በባንኩ ማኔጅመንት የተዘጋጀውና እ.አ.አ ከ2023/24 – 2027/28 የሚያገለግለው የባንኩን ስትራቴጂክ ዕቅድ ተወያይቶ በማፅደቅ ነው፡፡ አዲሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ የባንኩን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡
የፀደቀው ስትራቴጂክ ኘላን በየደረጃው የሚገኙ የባንኩ አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ጥልቅ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን፤ ስትራቴጂክ ዕቅዱን በብቃት ለማስፈፀም እንዲሁም የባንኩ ምርታማነትና ትርፋማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመዋቅር ማስተካከያና ማሻሻያ ይደረጋል፡፡
በተጨማሪም ያልተማከለ አሰራር በማስፈን የተጓደሉና አዳዲስ የሥራ መደቦች በፍጥነት በሰው ሃይል እንዲሟሉ እንደሚደረግም ታውቋል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!!