የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ አለም አስፋው በተገኙበት በባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና በትግራይ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ተወካይ ዶ/ር ተኸላይ አበበ መካከል ትናንት ማክሰኞ ነሐሴ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የስብሰባ አዳራሽ የተፈረመው ስምምነት ሁለቱም ተቋማት የጋራ በሆኑ ስራዎች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡
በስምምነቱ መሰረት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ኢንስቲትዩቱ በግብርና ምርምር ዘርፍ በሚያከናውናቸው ስራዎች ሁሉ አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅርቦት የሚሰጥ ሲሆን፤ ኢንስቶትዩቱም ለምርምር ስራው ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚያገኘውን ፋይናንስ አቅርቦት በአንበሳ ባንክ በኩል ያንቀሳቅሳል፡፡ የትግራይ ምርምር ግብርና ኢንስቲትዩት በገጠሩ ማሕበረሰብ ውስጥ ዘልቆ የሚሰራ እንደመሆኑ አንበሳ ባንክ በክልሉ ያለውን የቅርንጫፎች ቁጥርና ተደራሽነት ተቋሙ የባንክ አገልግሎትን በቅርበትና በቅልጥፍና ለማግኘት የሚያስችለው በመሆኑ አንበሳ ባንክ ተመራጭ ባንክ እንደሚያደርገው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
ለስምምነቱ መሳካት ሁለቱም ወገኖች በትጋት እንደሚሰሩም ተገልጿል፡፡