በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሐጎስ ዛሬ ነሐሴ 11 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የተፈረመው ስምምነት ሁለቱም ተቋማት በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በዚህም መሰረት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዩኒቨርሲቲው ለሚያካሂዳቸው ስራዎች አስፈላጊውን የፋይናንሻል አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፤ መቐለ ዩኒቨርሲቲም የባንኩን የሰው ኃይል አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችንና የቴክኒካል ድጋፍ ይሰጣል፡፡ ባንኩ ዩኒቨርሲቲው ለሚያስመርቃቸው ባለሙያዎች የስራ ዕድል በመፍጠር የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር !