*Announcement* Anbesa Bank has officially rebranded It's Identity.

(ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም) አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ስብሰባ በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ስብሰባውን የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ዳንኤል ተከስተ በንግግር ከፍተዋል፡፡
አቶ ዳንኤል ተከስተ በንግግራቸው ስብሰባው ውጤታማ እንዲሆን እና የባንኩን የወደፊት አቅጣጫ ለመቀየስ እንዲቻል ተሳታፊዎች ያልተቆጠበ ገንቢ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያበረታቱ ሲሆን የባንኩ የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም በባንኩ ፕላኒንግ እና ስትራቴጂ መምሪያ አጠቃላይ ሪፖርት ቀርቧል፡፡
ከዲስትሪክቶች በመጡ አመራሮች በቀረቡ የእቅድ እና አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ መድረኩ ውይይት ሲያደርግ በአበረታች አከናወኖች እና በአፈጻጸም ክፍተቶች ላይ ገንቢ አስተያየቶች ተሰጥዋል፡፡ ስብሰባው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!

Leave A Comment