*Announcement* Anbesa Bank has officially rebranded It's Identity.

(ጥቅምት 23፣ 2019 ዓ.ም)  አንበሳ ባንክ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በቮራ አዲስ ሆቴል አካሄደ።

ዛሬ በተካሄደው የሥራ አፈፃፀም ግምገማ በሐብት አስባሰብ፣ በውጭ ምንዛሬ ግኝት፣በዲጂታል ባንኪንግ እና በሌሎች መመዘኛዎች ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ተከስተ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ የተሻለ አፈፃፀም የነበራቸው መመዘኛዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና መሻሻል ያለባቸው መመዘኛዎች መስተካከል እንደሚኖርባቸው አፅንኦት በመስጠት ያልተጠናቀቁ የታቀዱ ሥራዎች እንዲከናወኑ  አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በግምገማው የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላትና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል።

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!