(ህዳር 5 ቀን 2019 ዓ.ም)አንበሳ ባንክ ላለፉት ዓመታት ባንኩን በቁርጠኝነትና በብቃት ላገለገሉ ነባር የቦርድ አባላት እውቅናና ምስጋና ለመስጠት፣ እንዲሁም ለአዳዲስ የቦርድ አባላት አቀባበል ለማድረግ በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል መርሐ ግብር አካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ተከስተ ነባር የቦርድ አባላት በአገልግሎት ዘመናቸው ላሳዩት ቁርጠኝነት፣ ታማኝነትና የበሰለ አመራር አድናቆታቸውን ገልጸዋል። አስተዋጽኦቸውም ለባንኩ ዕድገትና ስኬት ጠንካራ መሠረት መጣሉን አውስተዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው የዛሬው መርሐ ግብር የስንብት ሳይሆን፣ ነባር የቦርድ አባላት ያካበቱትን ልምድና ዕውቀት በማካፈል ከባንኩ ጎን ሆነው ድጋፋቸውን የሚቀጥሉበት አዲስ የትብብር ምዕራፍ መሆኑን አስታውቀዋል። ለአዳዲስ የቦርድ አባላትም መልካም የሥራ ዘመን በመመኘት፣ ከቀደሙት ተሞክሮ በመማር የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች በብስለት፣ በቆራጥነትና በአንድነት እንደሚሻገሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
