የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ አንቀጽ 367(1)፣ እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀፅ 11(7) መሰረት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክስዮኖች 20ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሠዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል። በመሆኑም ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተገኝተው በጉባዔው እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡
- ባንኩን የሚመለከቱ መረጃዎች
- የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥርያ ቤት አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ የካ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 014፣ የድረ-ገፅ አድራሻ: https://anbesabank.com
- የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡ MT/AA/3/0055690/2015
- የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡ ብር 3,149,681,061.70
- የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡ ብር 3,149,681,061.70
- የ20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- በቀረቡት የስብሰባ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል እና የአክሲዮን ዝውውር ማፅደቅ፣
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የጥቆማ እና የምርጫ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.ኤ.አ በ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
- እ.ኤ.አ የ2024/2025 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ወርሃዊ አበል መወሰን፣
- የባንኩ የውጪ ኦዲተር ሹመት ማፅደቅና ክፍያ መወሰን፣እና
- የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፣
- ማሳሰቢያ
- በጉባኤው ላይ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁን ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ ውክልና ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት 22 ማዞሪያ ሌክስ ፕላዛ ህንፃ ውስጥ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 707 በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅፅ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ መሆንና ድምጽ መስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
- የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ቅጂ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
- ለምዝገባ ቅልጥፍና ሲባል ባንኩ የባለአክስዮኖችን የመለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት የተንቀሳቃሽ ስልክ መልዕክት የሚላክላችሁ ሲሆን፤ የመለያ ቁጥራችሁን በስብሰባው ዕለት ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
አንበሳ አንተርናሽናል ባንክ ለረጅም ዓመታት አብረውት ሲሰሩ ለቆዩ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ደንበኞቹ የምስጋና እና የእውቅና ሽልማት የመስጠት ቀን አከበረ።
ባንኩ ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው የምስጋናና የዕውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም በወጪ ንግድ፣ በአለም አቀፍ ሐዋላ አገልግሎት፣ በቴሌኮም እና በልዩ ልዩ ዘርፍ ተሠማርተው ለባንኩ የውጪ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ከ37 በላይ ደንበኞች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ሽልማት ሰጥቷል።
ባንኩ በተጠናቀቀው የበጀት አመት በወጪ ንግድ የተሠማሩ ደንበኞችን የፋይናንስ አቅርቦት ለማሟላት ከፍተኛ እገዛ ያደረገ ከስምንት ቢልዮን ብር በላይ ሃብት ማሰባቡን የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ገልፀዋል።
የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አሰፋው በበኩላቸው ለረጅም አመታት አብረው ሲሰሩ ለቆዩ ደንበኞች ምስጋና አቅርበው፧ ደንበኞች ባንኩ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ መክር እና አሰተያየት እንዲሰጡ ባቁረቡት ጥሪ መሠረት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በተደረገው ውይይት በአሁኑ ሠዓት መንግስት ስራ ላይ ያዋለውን የፋይናንሻል ፖሊሲ መሠረት በርካታ የውጭ ባንኮች ወደ ገበያ መግባታቸው ስለማይቀር ኤክስፖርተሮችን ለመያዝ ራሱን ማዘጋጀት እንደሚጠበቅበት አመልክተዋል።
በተለይም ለውጪ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ላኪዎችን ለመያዝ እና ተወዳዳሪ ባንክ ሆኖ ለመዝለቅ በውጭ ምንዛሪ ድርድር ላይ ብልሃት የተሞላበት ስራ ሊሰራ አንደሚገባ ተጠቁሟል።
ባንኩ በበኩሉ የደንበኞቹን የፋይናንስ አቅርቦት ለመመለስ የሚያስችል አቅም ፈጥሮና በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።
በቴክኖሎጂ ረገድም የወጪ ንግድን ለማገዝ የሚያስችል መሠረተ ልማት በመዘርጋት ላይ በመሆኑ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት እንደሚሰራ ተገልጿል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና እልፍ ብድር እና ቁጠባ ሕብረት ማህበር በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና እልፍ ብድር እና ቁጠባ ሕብረት ማህበር አገልግሎታቸውን በኦንላይን ማስተሳሰር የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡
በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት በአቶ ዳንኤል ተከስተ እና እልፍ ብድር እና ቁጠባ ሕብረት ማህበር የቦርድ ዳይሬክተር የሆኑት በወ/ሮ የምወድሽ በቀለ የተፈረመው ስምምነት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደንበኞች ወደ እልፍ ብድር እና ቁጠባ ሕብረት ማህበር ሂሳባቸው ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን ለማናበብ በሁለቱ ተቋማት መካከል ይደረግ የነበረውን የወረቀት ልውውጥና ድካም ለማስቀረት ከማስቻሉም በላይ ደንበኞች በስራ ቦታቸው ሆነው ገንዘባቸውን በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እንዲያስተላልፉ በማድረግ የስራ ቅልጥፍናን የሚያጎለብት ነው፡፡
በዚህም መሰረት የብድር እና ቁጠባ ማህበሩ አባላት ወርሀዊ ቁጠባቸውንም ሆነ የብድር ክፍያቸውን ወደ ተቋሙ ቢሮ መሄድ ሳይጠበቅባቸው በአንበሳ ባንክ የመደበኛ እና ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች በኩል ገቢ ሲያደርጉ ወዲያውኑ የሁሉ ወደሚገኘው ሂሣባቸው የሚተላለፍ ሲሆን፤ በዚያው ቅፅበትም የባንኩንና እልፍ ብድር እና ቁጠባ ሕብረት ማህበር ሂሣቦች ዲጂታል በሆነ መንገድ የማስታረቅና የማወራረድ ሥራ ይሰራል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል እልፍ ብድር እና ቁጠባ ሕብረት ማህበር የሚያደርገውን የቴክኖሎጂ ትስስር አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ድጋፍ እንደሚያደርግና ተቋሙ የብድር አቅርቦት ሲያስፈልገው ባንኩ የብድር አቅርቦቱን እንደሚያመቻች ተገልጿል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር !
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የመቐለ ህንፃ መሳሪያ ማሕበር የገበያ ማዕከል በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት አደረጉ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከመቐለ ህንፃ መሳሪያ ማሕበር የገበያ ማዕከል ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት የሚያስችላቸው የፊርማ ሰነ- ሰርአት ስምምነት ዛሬ ጳጉሜን 3 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ አክሱም ሆቴል አካሂደዋል። የፊርማ ስነ-ስርአቱ በባንኩ ፕሬዝዳንት በአቶ ዳንኤል ተከስተ እና በማሕበሩ ሊቀ መንበር አቶ ገብሩ ተኽሉ ተካሂዷል።
ይህ የፊርማ ሰነ- ስርአት የተካሄደው ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት እና 422 አባላቱ በተገኙበት ሲሆን፤ ማሕበሩ በመቐለ ከተማ እያስገነባ ባለው የገበያ ማዕከል ግንባታ ላይ ባንኩ ሙሉ የፋይናንሰ አቅርቦት እንደሚያደርግ እና የማሕበሩ አባላቶችም የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በአንበሳ ባንክ ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ የክልሉን የኢኮኖሚ ተሳትፎ በሙሉ አቅሙ ለመደገፍ እና የመልሶ ግንባታ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የራሱን አስተዋፅኦ እያደረገ ሲሆን፤ በሚደርገው የልማት ርብርብ ላይ የንግዱ ማሕበረሰብ አባላት በተለይም የዚህ ማሕበር አባላት በሙሉ አቅማቸው ከባንኩ ጎን እንዲቆሙ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከሰተ ጥሪ አቅርበዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የአዲስ አበባ፣ሃዋሳ እና የአዳማ ዲስትሪክቶች አመታዊ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።
የባንኩ አመታዊ የአፈፃፀም ግምገማ በአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል፣በአዳማ ደብል ቪው ሆቴል እንዲሁም በሃዋሳ ሴንተራል ሃዋሳ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፤ አጠቃላይ የባንኩ እና የየዲስትሪክቶቹ የ2023/24 በጀት ዓመት አመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ዲስትሪክቶቹ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በሁሉም የአፈፃፀም መለኪያዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላት እና በየዲስትሪክቶቹ የሚገኙ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የተገኙ ሲሆን፤ በቀረበው ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ውይይት ተደርጓል፡፡ በቀጣይ በጀትም በዘንድሮው በጀት አመት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ውጤት መቀየር እንደሚኖርባቸው እና ከዘንድሮው በተሻለ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባው ተጠናቋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና መሓዙት ቁጠባ እና ብድር ሕ/ሥ/ማህበር ኃ.የተወሰነ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና መሓዙት ቁጠባ እና ብድር ሕ/ሥ/ማህበር ኃ.የተወሰነ አገልግሎታቸውን በኦንላይን ማስተሳሰር የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን፤ የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የሰሜን ሪጅን ፅ/ቤት ም/ፕሬዝዳንት አቶ አክሊሉ ሓየሎም እና መሓዙት ቁጠባ እና ብድር ሕ/ሥ/ማህበር ኃ.የተወሰነ የቦርድ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብርሃለይ ተኽለማርያም ተቋሞቻቸውን በመወከል የጋራ ስምምነቱን ፈርመዋል። ስምምነቱ የሁለቱን ተቋማት የጋራ እድገት የሚያረጋግጥ መሆኑን በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር !
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ሕ/ሥ/ማህበር ኃ.የተወሰነ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ሕ/ሥ/ማህበር ኃ.የተወሰነ አገልግሎታቸውን በኦንላይን ማስተሳሰር የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡
በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና በየሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ሕ/ሥ/ማህበር ኃ.የተወሰነ የቦርድ ዳይሬክተር እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ መሳፍንት ደበበ የተፈረመው ስምምነት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደንበኞች ወደ የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ማህበር ሂሳባቸው ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን ለማናበብ በሁለቱ ተቋማት መካከል ይደረግ የነበረውን ውጣ ውረድ ለማስቀረት ከማስቻሉም በላይ ደንበኞች ካሉበት ቦታ ሆነው ገንዘባቸውን በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እንዲያስተላልፉ በማድረግ የስራ ቅልጥፍናን የሚያጎለብት ነው፡፡
በዚህም መሰረት የህብረት ሥራ ማህበሩ አባላት ወርሀዊ ቁጠባቸውንም ሆነ የብድር ክፍያቸውን በአንበሳ ባንክ የመደበኛ እና ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች በኩል ገቢ ሲያደርጉ ወዲያውኑ የሁሉ ወደሚገኘው ሂሣባቸው የሚተላለፍ ሲሆን፤ የባንኩንና የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ማህበሩ ሂሣቦች ዲጂታል በሆነ መንገድ የማስታረቅና የማወራረድ ሥራ ይሰራል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለደንበኞች የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል የሁሉ ገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ማህበር የሚያደርገውን የቴክኖሎጂ ትስስር አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ድጋፍ እንደሚያደርግና ማህበሩ የብድር አቅርቦት ሲያስፈልገው ባንኩ የብድር አቅርቦቱን እንደሚያመቻች ተገልጿል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር !
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና የትግራይ ክልል ሕ/ስ/ማህበርና ገበያ ልማት ኤጀንሲ በጋር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና በትግራይ ክልል የሚገኙ የህብረት ስራ ማህበርና ገበያ ልማት ኤጀንሲ በጋር ለመስራት የሚያስቸላቸውን የመግባብያ ስምምነት ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ በደስታ ሆቴል ተፈራረሙ። የትግራይ ክልል ሕብረት ስራ ኤጀንሲ በትግራይ ክልል በተለያየ ዘርፍ የተሰማሩ ከ65 በላይ የሕ/ስ/ማሕበራት ዩኒየኖችን በማደራጀት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፤ ማህበሩ በአጠቃላይ ከ1.33 ሚሊዮን በላይ አባላት ሲኖሩት ከ476 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 5,274 ማሕበራትን አደራጅቶ እየሰራ ያለ ግዙፍ ተቋም ነው።
ስምምነቱ በአንበሳ ባንክ ፕሬዝዳንት በአቶ ዳንኤል ተከስተ እና በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋ አሰፋ የተፈረመ ሲሆን፤ በዚሁ ዕለት ከሁሉም የክልሉ ወረዳዎች ከመጡ የ65 ሕ/ስ/ማሕበራት ዩኒየኖች የስራ ኃላፊዎች ጋር የምክክር ስብሰባ ተካሂዷል፡፡ ይህ ስምምነት ሲፈፀም በተናጠል ከመስራት ይልቅ በመደጋገፍና በመተባበር ላይ የተመሰረተ የተቀናጀ ስራ መስራት የሁለቱንም ተቋሞች የጋራ ፍላጎትና ዓላማ ከማሳካት ኣኳያ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር !
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት እና የዳይሬክተሮች ቦርድ በሀዋሳ ከተማ ከሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ከሆኑ ደንበኞች ጋር በባንኩ አገልግሎት ዙሪያ ምክክር እና የፋብሪካዎች ጉብኝት አካሄዱ።
በባንኩ ፕሬዝዳንት በአቶ ዳንኤል ተከስተ እና በዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አስፋው የተመራው ቡድን ከማክሰኞ ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ ከሚገኙ ደንበኞች ጋር ባካሄደው ውይይት ባንኩ እየሰጣቸው ባሉ አገልግሎቶች ዙሪያ እና የንግዱን ማህበረስብ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በሳውዝ ስታር ሆቴል በተካሄደው ውይይት ባንኩ ደንበኞች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ አስፈላጊውን የፋይናንስ አቅርቦት ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት ሲገልፅ ፤ የንግድ ማህበረሰቡም ከባንኩ ጋር አብረው ለመስራት ዝግጁነታቸውን አሳውቀዋል።
ከውይይቱ ጎን ለጎንም የዳይሬክተሮች ቦርድና የማኔጅመንት ቡድኑ በሀዋሳ ከተማ በመስራት ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎች፣ አምራች ድርጅቶች እና የብድር እና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራትን የጎበኘ ሲሆን፤ ፋብሪካዎቹ እያደረጉ ያለው አበረታች የምርታማነት ስራ ለመደገፍ ባንኩ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ፤ እንዲሁም ከብድር እና ህብረት ስራ ማህበራቱ ጋር በአጋርነት ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ እና ጉብኝቱ ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጥሏል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በማሳደግ ዙሪያ ከከፍተኛ ባለአክስዮኖች ጋር ምክክር አካሄዱ።
የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል ለማሳደግ ከባለአክስዮኖች ጋር ሲያደርግ የነበረውን ምክክር አካል የሆነውን ስብሰባ ከከፍተኛ ባለአክስዮኖች ጋር ትናንት ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል አካሂዷል። በምክክር መድረኩ ከፍተኛ ባለአክስዮኖቹ ተጨማሪ አዲስ አክስዮኖችን መግዛትና የባንኩን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት በሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
ውይይቱ ባንኩ በሁሉም የመመዘኛ መስፈርቶች ብቁ እና ተወዳዳሪ ለመሆን በሚያደርገው ጉዞ ላይ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው የተገለፀ ሲሆን፣ ከፍተኛ ባለአክሰዮኖች ተጨማሪ አዳዲስ አክሲዮኖችን እንደሚገዙ እና ሌሎች ደንበኞችንም አክስዮን እንዲገዙ ለማድረግ እንደሚሰሩ አመልክተዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የአዲስ አበባ፣ሃዋሳ እና የአዳማ ዲስትሪክቶች አመታዊ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ።
የባንኩ አመታዊ የአፈፃፀም ግምገማ በአዲስ አበባ አክሱም ሆቴል፣በአዳማ ደብል ቪው ሆቴል እንዲሁም በሃዋሳ ሴንተራል ሃዋሳ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፤ አጠቃላይ የባንኩ እና የየዲስትሪክቶቹ የ2023/24 በጀት ዓመት አመታዊ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ዲስትሪክቶቹ ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በሁሉም የአፈፃፀም መለኪያዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ከፍተኛ የስራ አመራር አባላት እና በየዲስትሪክቶቹ የሚገኙ የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች የተገኙ ሲሆን፤ በቀረበው ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ውይይት ተደርጓል፡፡ በቀጣይ በጀትም በዘንድሮው በጀት አመት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ወደ ውጤት መቀየር እንደሚኖርባቸው እና ከዘንድሮው በተሻለ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባው ተጠናቋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የመቐለ፣ አክሱም እና ማይጨው ዲስትሪክቶች የዘጠኝ ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄዱ።
የማይጨው ዲስትሪክት በማይጨው ከተማ ታደለ ሆቴል ፣ የአክሱም ዲስትሪክት በአክሱም ከተማ ሳቢያን ሆቴል እንዲሁም የመቐለ ዲስትሪክት መቐለ ከተማ በዓምድና ሆቴል የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር አፈጻጸም ግምገማ ዛሬ ረቡዕ ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ያካሄዱ ሲሆን፤፤ የሦስቱ የዲስትሪክት ሥራ አስኪያጆች ከዋና መስሪያ ቤት አመራሮች ጋር በአፈጻጸም ሂደት ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ውይይት እና የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ሦስቱ ዲስትሪክቶች በ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር አፈጻጸም የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ ላይም ዲስትሪክቶቹ በቀሪው የበጀት ዓመት እቅዳቸውን ለማሳካት በተሻለ መልኩ እንደሚያከናውኑ ገልፀዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!
በሀዋሳ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት አባላት በሀዋሳ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች ጋር በ2016 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በሀዋሳ ሳውዝ ስታር ሆቴል አካሄዱ፡፡ በስብሰባው የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በሁሉም ቅርንጫፎች አፈጻጸም ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡በዚህም በቀሪው የበጀት ዓመት የተያዙ ግቦችን ለማሳካት…
በአዳማ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት አባላት በአዳማ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች ጋር በ2016 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ድሬ ኢንተርናሽናል ሆቴል አካሄዱ፡፡ በስብሰባው የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በሁሉም ቅርንጫፎች አፈጻጸም ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡በዚህም በቀሪው የበጀት ዓመት የተያዙ ግቦችን ለማሳካት…
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በባንኩ ካፒታል ማሳደግ ዙሪያ ከባለአክስዮኖች ጋር ምክክር አካሄዱ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን ለማሳደግ በማሰብ ከከፍተኛ ባለአክስዮኖች ጋር ዛሬ ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል አካሂዷል።በተዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የባንኩ አጠቃላይ እንቅስቃሴ የቀረበ ሲሆን የባንኩን የተከፈለ ካፒታል ማሳደግ፣ አክስዮኖችን መግዛትና የባንኩን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበት እንደሚሰሩ ገልፀዋል። አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የስኬትዎ አጋር!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከሚያዝያ 12-19 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ “የትግራይ “ህብረት ባዛር እና ኤግዚብሽን” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ባዛር እና ኤግዚብሽን በፕላቲኒየም ደረጃ ስፓንሰር አደረገ።
ላለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ከሰው ህይወት በዘለለ በኢኮኖሚው ላይ በርካታ ጉዳት ደርሷል፡፡ በተጨማሪም በክልሉ በርካታ አከባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሰብል ነክ የአቅርቦት ችግር ተከስቷል። ይህንን ለመቅረፍ የትግራይ ክልል የህብረት ስራ እና ገበያ ልማት ኤጀንሲ በመቐለ ከተማ ከሚያዝያ 12-19 ቀን 2016 ዓ.ም ለስምንት (8) ቀናት የሚቆይ ሃገር…
ለአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለአክስዮኖች የተላለፈ የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ
ለአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለአክስዮኖች የተላለፈ የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው የባለአክስዮኖች 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩ ካፒታል ወደ ብር 10 ቢልየን እንዲያድግ መወሰኑ ይታወቃል። ስለሆነም ለሽያጭ እንዲቀርብ ከተፈቀደው ካፒታል ውስጥ ነባር ባለአክስዮኖች ባላቸው የቀደምትነት መብት መሰረት በመጀመሪያ ዙር ለሽያጭ የቀረበውን አክስዮን እንዲገዙ ባላቸው አክስዮን መጠን ድልድል ተደርጓል። በዚሁ መሰረት የባንኩ ነባር…
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ቫይት ቴክኖሎጂስ የባንኩን የክፍያ ስርዓት ለማዘመን በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና በቫይት ቴክኖሎጂስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ገ/ኪዳን ገ/መድህን ዛሬ ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ የተፈረመው ስምምነት የባንኩን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለማጎልበት እና የክፍያ ስርዓትን በማዘመን ደንበኞች የትምህርት ቤት፣ የውሃ እና የመዘጋጃ ቤት አገልግሎት ክፍያዎችን በኤሌክትሮኒክስ አሰራር መክፈል የሚችሉበትን ስርዓት መዘርጋት እንዲሁም የባንኩን የዳታ አያያዝና የደህንነት ስርዓትን…
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የአክሱም እና የእንዳስላሰ ዲስትሪክቶች አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት በአክሱም እና እንዳስላሰ ዲስትሪክቶች የሚገኙ ቅርንፎች የ2016 የመጀመሪያ ሩብ የበጀት አመት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በአክሱም ኮንሱላር ሆቴል በተካሄደ የእቅድ ክንውን ግምገማ ሁለቱም ዲስትሪክቶች አበረታች አፈጻጸም ማሰመዝገባቸውን ማረጋገጥ ተችሏል። በዲስትሪክቶቹ ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች ያሳዩት አበራታች ጥረት ለአካባቢው የንግድ እነቅስቃሴ መነቃቃት ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆኑን ማኔጅመንት…
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የመቐለ፣ ዓዲግራት እና ማይጨው ዲስትሪክቶች አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት በመቐለ፣ ዓዲግራት እና ማይጨው ዲስትሪክቶች የሚገኙ ቅርንፎች የ2016 የመጀመሪያ ሩብ የበጀት አመት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ። ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ዓዲግራት እና ማይጨው ከተሞች በተካሄደ የእቅድ ክንውን ግምገማ ሦስቱም ዲስትሪክቶች ከእቅዳቸው በእጅጉ የበለጠ አፈጻጸም ማሰመዝገባቸውን ተመልክቷል። በዚህም አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በክልሉ እየተነቃቃ በመምጣት ላይ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ በመደገፍ ረገድ…
በሐዋሳ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የአፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት በሐዋሳ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች ጋር በ2016 የመጀሪያ ሩብ የበጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡ዛሬ ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም በሐዋሳ ሳውዝ ስታር ሆቴል በተካሄደ ግምገማ በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፈጻጸም ላይ በታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡የሩብ የበጀት ዓመቱ ግምገማ…
በአዳማ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የአፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት በአዳማ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች ጋር በ2016 የመጀሪያ ሩብ የበጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡ዛሬ ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ናፍሌት ሆቴል በተካሄደ ግምገማ በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ 22 ቅርንጫፎች የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፈጻጸም ላይ በታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡ቅርንጫፎቹ በሩብ የበጀት ዓመቱ…
በአዲስ አበባ ሪጅን የሚገኙ ዲስትሪክቶች አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ሲንየር ኤክዘክዩቲቭ ማኔጅመንት በአዲስ አበባ ሪጅን ስር ከሚገኙ ዲስትሪክቶች ጋር በ2016 የመጀሪያ ሩብ የበጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡ትናንት መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው ግምገማ በአዲስ አበባ ሪጅን ስር የሚገኙ አምስት ዲስትሪክቶች የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፈጻጸም ላይ በታዩ ጠንካራ እና ደካማ…
የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ማኔጅመንት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁሉም ሠራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ፕሮግራም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አስፋው ለሁሉም የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች የሰላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆንላቸው በመመኘት በአዲሱ ዓመት ባንኩን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩበት ጊዜ እንደሚሆን ገልፀዋል። ባንኩ ከምንጊዜውም ይበልጥ በርካታ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየሰራ በመሆኑ አሁን ላይ ህብረተሰቡ ለባንኩ ያለው አመለካከት ከሚጠበቀው በላይ አበረታች ስለሆነ ይህን…