News

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ “Anbesa Fund” ’የተባለ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ፕላትፎርም ስራ ላይ አዋለ

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ትረስትድ ቴክ ከተሰኘ የቴክኖሎጂ አቅራቢ ደርጅት ጋር በመተባበር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ በሀገር ውስጥ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችል ‘Anbesa Fund’ ’የተባለ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ቴክኖሎጂውን በይፋ አስመርቆ ስራ ጀመረ፡፡
 
ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ተመርቆ ወደ ትግበራ የገባው ‘Anbesa Fund’  የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ፕላት ፎርም በሃገራችን በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሳቢያ የወደሙ ማህበራዊ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የህብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታት ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ የዲያስፖራውን የገንዘብ ድጋፍ ተሳትፎ የሚጠይቁ ስራዎችን ለማሳለጥ ይረዳል፡፡
 
 በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ የነበረውን ጦነት በሠላም መፈታትን ተከትሎ ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የወደሙ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የመልሶ ግንባታ ስራዎች ለማከናወን ከዲያስፖራ ማህበረሰብ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክቶችን ቀርፀው ገንዘብ ለማሳባሰብ ዕቅድና ፍላጎት ያላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንበሳ ባንክ ያዘጋጀውን አንበሳ ፈንድ (Anbesa Fund platform) ተጠቅመው ገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ለማካናወን አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው ይታመናል፡፡
 
አንበሳ ፈንድ (Anbesa Fund) የእርዳታ ማሰባሰቢያ platform ድረ-ገፅን መሰረት አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሞባይል ስልኮቻችውም ሆነ በሌሎች የትስስር ገፆቻቸው አማካኝነት ወደ አንበሳ ፈንድ ድረ-ገፅ www.anbesafund.com በቀላሉ ገብተው የፈለጉትን ያህል የገንዘብ ልገሳ በማድረግ በሀገራቸው ልማት ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ለመሆን ያስችላቸዋል፡፡
 
አንበሳ ፈንድ የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕላት ፎርም በአሁኑ ሰዓት ሙሉ የፍተሻ እና የሙከራ ስራው ተጠናቆለት ለትግበራ ዝግጁ የሆነ ሲሆን፤ የተጠቃሚ ደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በኦንላይን የአክስዮን ሽያጭ ማከናወኛ ፕላት ፎርም በማከል ልዩ ልዩ የቢዝነስ ፕሮጀክቶችን ቀርፀው አክስዮኖችን መሸጥ ለሚፈልጉ የስራ ፈጣሪዎችም አመቺ መድረክ ለመፍጠር ይሰራል፡፡ አንበሳ ባንክ በቀጣይ ወደ ተግበራ የሚያስገባው በኦንላይን የአክስዮን መሸጫ ፕላትፎርም በሀገራችን ወደ ትግበራ እየገባ ላላው የStock market የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግም ተስፋ እናደርጋለን፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ስራ ጀመረ

በ18ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ መደበኛ ስራውን ጀመረ፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርዱ ቅዳሜ ሰኔ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ስራውን የጀመረው አዲስ ሊቀ-መንበር እና ምክትል ሊቀ-መንበር በመምረጥ ሲሆን፤ አቶ አለም አስፋውን ሊቀ-መንበር፤ ዶ/ር አክሊሉ ገ/ስላሴን ደግሞ ምክትል ሊቀ-መንበር አድርጎ መርጧል፡፡ ቦርዱ በተጨማሪም ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችሉት ሦስት ንኡሳን ኮሚቴዎችን አዋቅሯል፡፡

ቦርዱ የመጀመሪያ ስራውን ያደረገው በባንኩ ማኔጅመንት የተዘጋጀውና እ.አ.አ ከ2023/24 – 2027/28 የሚያገለግለው የባንኩን ስትራቴጂክ ዕቅድ ተወያይቶ በማፅደቅ ነው፡፡ አዲሱ ስትራቴጂክ ዕቅድ የባንኩን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማፋጠን እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡

የፀደቀው ስትራቴጂክ ኘላን በየደረጃው የሚገኙ የባንኩ አመራሮችና ሠራተኞች ጋር ጥልቅ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን፤ ስትራቴጂክ ዕቅዱን በብቃት ለማስፈፀም እንዲሁም የባንኩ ምርታማነትና ትርፋማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የመዋቅር ማስተካከያና ማሻሻያ ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም ያልተማከለ አሰራር በማስፈን የተጓደሉና አዳዲስ የሥራ መደቦች በፍጥነት በሰው ሃይል እንዲሟሉ እንደሚደረግም ታውቋል፡፡  

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር!!

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በትግራይ ክልል በጦርነት ምክንያት የወደሙ ማህበራዊ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ለትግራይ ልማት ማህበር የ100 ሚልየን ብር ድጋፍ ሰጠ።

ባንኩ የ100 ሚልየን ብር ደጋፍ የሰጠው ከትግራይ ልማት ማህበር ጋር ዘላቂ የሆነ አጋርነትና አብሮ የመስራት ስምምነት ትናንት ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በመቐለ ፕላኔት ሆቴል በተፈራረሙበት ጊዜ ነው።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ የድጋፍ ገንዘቡን ሲያስረክቡ እንደተናገሩት በጦርነቱ ምክንያት በክልሉ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና በህብረተሰቡ ስነ- ልቦና ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት ደርሷል። ስለሆነም ህብረተሰቡን ከዚህ ጉዳቱ ፈጥኖ እንዲያገግም ለማድረግ እና ተቋማት መልሰው መገንባትና ለአገልግሎት መብቃት መቻል አለባቸው በማለት ገልፀዋል።

በዚህም መሰረት አንበሳ ባንክ ለመልሶ ግንባታ ሰራዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚቀርብለትን የድጋፍ ጥያቄ በአንድ ጊዜ ምላሽ መስጠት ስለማይችል በትግራይ ልማት ማህበር በኩል ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆኑ ስራዎችን መስራት አማሬጭ አድርጎ ወስዶታል።

አንበሳ ባንክ የሰጠው የ100 ሚልየን ብር ድጋፍ በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው።

የትግራይ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋየ ገ/ እግዚአብሔር በበኩላቸው ክልሉን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አንበሳ ባንክ ቀዳሚ በመሆን የአንበሳ ድርሻውን መወጣቱን ገልፀው፤ ከባንኩ ድጋፍ የተገኘው ገንዘብ ለቃላሚኖ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልሶ ግንባታና ስራ ማስጀመሪያ ይውላል ብለዋል።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በመቐለ ከተማ ከ90 በላይ አባል ማህበራትን አቅፎ በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኘው ጮምዓ የብድርና ቁጠባ ማህበራት ዩኒየን ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ።

ትናንት ዓርብ ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በመቐለ ፕላኔት ሆቴል በተካሄደው የስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከሰተ እንደገለፁት ከጮምዓ የብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ጋር አብሮ መስራት ያስፈለገው በስሩ ለሚገኙ ከ90 በላይ አባል የብድርና ቁጠባ ማህበራትና ከ87 ሺህ በላይ አባላቱን ተደራሽ ለመሆን ነው።
ዩኒየኑ የአባል ማህበራቱን አቅም ለማጎልበት በሚያደርገው ጥረት አንበሳ ባንክ የብድርና የፋይናንስ አቅርቦት ለመስጠት እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና በዓቅም ግንባታ ስልጠናዎች አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል።
የጮምዓ ብድርና ቁጠባ ማህበራት ዩኒየን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ ህይወት ኪዳነ በበኩላቸው ዪኒየኑ በስሩ የሚገኙ ከ 87 ሺህ በላይ አባላቱን ከአንበሳ ባንክ ጋር እንዲሰሩ ትስስር ለመፍጠር ያስችለዋል ብለዋል።
ጮምዓ ዩኒየን በአሁኑ ሰዓት ከ90 በላይ ማህበራትና 76,296 አባላት ይዞ በመቐለ ከተማ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን፤ ከ67 ሚልየን ብር በላይ ካፒታል አለው ::

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በትግራይ ክልል በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ የጦር ጉዳተኞች ማቋቋሚያ የሚሆን የ2 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እርዳታውን ትናንት በመቐለ ፕላኔት ሆቴል ለትግራይ ጦር ጉዳተኞች ማህበር ሲያስረክቡ እንደገለፁት ባንኩ በጦርነቱ ምክንያት አካላቸው የጎደለ ወገኖችን በመደገፍ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ያስችለዋል።
የትግራይ ጦር ጉዳተኞች ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጨርቆስ ወ/ ማርያም በበኩላቸው ስለተደረገው እርዳታ አመስግነው፣ የተገኘው ገንዘብ በጦርነቱ ምክንያት ከምዕራብ ትግራይ ተፈናቅለው በሽረ እንዳስላሰ የሚገኙ አካል ጉዳተኛ ተፈናቃዮችን ለማገዝ ይውላል ብለዋል።

https://linktr.ee/anbesabank

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ያለ ዋስትና ማስያዣ ለመስጠት የሚያስችለው መተግበሪያ ዛሬ በይፋ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በደመወዝ ለሚተዳደሩ እና በአነስተኛ የገቢ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትት ከምንም ዓይነት የዋስትና ማስያዣ ነፃ የሆነ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው መተግበሪያ ዛሬ በይፋ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ለዚህ የብድር አገልግሎት የሚውል 500 ሚልየን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ መመደቡንም አስታውቋል፡፡

በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና መተግበሪያውን ባበለፀገው ሀገር በቀል ድርጅት በሆነው ኳንተም ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሶፎንያስ እምቢበል ዛሬ በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የተመረቀው አለኝታ የተሰኘ ዲጂታል የብድር አገልግሎት በባንኩ የቁጠባ ሒሳብ ያለው ማንኛውም ደንበኛ ወደ ባንኩ በአካል መቅረብም ሆነ የብድር ዋስትና ማስያዝ ሳያስፈልገው በእጁ ባለው ሞባይል ብቻ በመጠቀም ብድር ማግኘት የሚያስችለው አሰራር ነው፡፡

የአለኝታ ዲጂታል ብድር አቅርቦት መተግበሪያን ያበለፀገው የኳንተም ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሶፎንያስ እምቢበል በበኩላቸው ኩባንያቸው ከአንበሳ ባንክ ጋር በፈጠረው አጋርነት የባንኩን የዲጂታል ብድር አቅርቦት አሰራርን መሰረት በማድረግ ለደንበኞች ቀላልና ምቹ የሆነ መተግበሪያ አዘጋጅቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን ገልጸዋል፡፡

ኳንተም ቴክኖሎጂ በዕድሜ ገና ወጣት ቢሆንም ከምስረታው ጀምሮ በኮምፒውተር ሳይንስና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የካበተ ልምድና ክህሎት ባላቸው ባለሙያዎች ስብስብ የተቋቋመ ሲሆን፤ የሀገራችንን E-Payment ስርዓትን ወደ ፊት ሊያራምዱ የሚችሉ ስራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር!

https://linktr.ee/anbesabank

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና አዋጭ የገ/ቁ/ብ/መ/የህ/ሥ/ማህበር  በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና አዋጭ የገ/ቁ/ብ/መ/የህ/ሥ/ማህበር አገልግሎታቸውን በኦንላይን ማስተሳሰር የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡
በአዋጭ የገ/ቁ/ብ/መ/የህ/ሥ/ማህበር የኮር ባንኪንግ እና ሶፍትዌር ማስፋፊያ ኃላፊ በሆኑት አቶ ሰለሞን ወሌ እና በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሰሎሞን ተስፋዬ የተፈረመው ስምምነት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ደንበኞች ወደ አዋጭ የገ/ቁ/ብ/መ/የህ/ሥ/ማህበር ሂሳባቸው ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ የሂሳብ እንቅስቃሴያቸውን ለማናበብ በሁለቱ ተቋማት መካከል ይደረግ የነበረውን የወረቀት ልውውጥና ድካም ለማስቀረት ከማስቻሉም በላይ ደንበኞች በስራ ቦታቸው ሆነው ገንዘባቸውን በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እንዲያስተላልፉ በማድረግ የስራ ቅልጥፍናን የሚያጎለብት ነው፡፡ 
በዚህም መሰረት የህብረት ሥራ ማህበሩ አባላት ወርሀዊ ቁጠባቸውንም ሆነ የብድር ክፍያቸውን በአንበሳ ባንክ የመደበኛ እና ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች በኩል ገቢ ሲያደርጉ ወዲያውኑ አዋጭ ወደሚገኘው ሂሣባቸው የሚተላለፍ ሲሆን፤ በዚያው ቅፅበትም የባንኩንና የአዋጭ ህብረት ሥራ ማህበሩ ሂሣቦች ዲጂታል በሆነ መንገድ የማስታረቅና የማወራረድ ሥራ ይሰራል፡፡
 
                              አንበሳ ኢንተርናሽል ባንክ
                                   የስኬትዎ አጋር !

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ሲንየር ኤክዘኪዩቲቭ ማኔጅመንት በትግራይ ክልል የሚገኙ ቅርንጫፎቹን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በሰሜን ሪጅን ከሚገኙ የባንኩ ሠራተኞች ጋር ውይይት አካሄደ።

ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በሞሞና ሆቴል በተደረገ ውይይት በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ቅርንጫፎች መልሶ በማቋቋም በተቻለ ፍጥነት ወደ ስራ ማስገባት እንዲሁም አሁን የተጀመረው የባንክ አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።
በተጨማሪም ባንኩ አሁን እየሰጠ ካለው ጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሰረተ አገልግሎት በተጨማሪ በክልሉ የቴሌ ኔትዎርክ አገልግሎ መስጠት በጀመረባቸው አከባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች ባንኩ ሰራ ላይ ያዋለውን የዲጂታል ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማሳወቅ ስራ በስፋት መሰራት እንዳለበት ተመልክቷል።
በትግራይ ክልል አሁን ካለው የጥሬ ገንዘብ (ካሽ) እጥረት አንፃር ደንበኞች የአንበሳ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን በመጠቀም ከባንኩ ሂሳብ ወደ ሌላ ሂሳብ ማዛወር፣ ማንኛውም አይነት ግብይት መፈፀም እና ክፍያዎችን ማከናወን ይችላሉ።

በሐዋሳ ዲስትሪክት ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የአፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት በሐዋሳ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች ጋር በ2016 የመጀሪያ ሩብ የበጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡
ዛሬ ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም በሐዋሳ ሳውዝ ስታር ሆቴል በተካሄደ ግምገማ በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ ቅርንጫፎች የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፈጻጸም ላይ በታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡
የሩብ የበጀት ዓመቱ ግምገማ በአፈፃፀም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የታለመ ነው፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የመቐለ፣ ዓዲግራት እና ማይጨው ዲስትሪክቶች አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት በመቐለ፣ ዓዲግራት እና ማይጨው ዲስትሪክቶች የሚገኙ ቅርንፎች የ2016 የመጀመሪያ ሩብ የበጀት አመት አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።

ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ፣ ዓዲግራት እና ማይጨው ከተሞች በተካሄደ የእቅድ ክንውን ግምገማ ሦስቱም ዲስትሪክቶች ከእቅዳቸው በእጅጉ የበለጠ አፈጻጸም ማሰመዝገባቸውን ተመልክቷል።

በዚህም አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በክልሉ እየተነቃቃ በመምጣት ላይ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ በመደገፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

Anbesa School Pay

Contact Us

Tel: (+251) 11 662 60 00/60
Fax: (+251) 11 662 59 99
P.O.Box: 27026/1000 Addis Ababa
E-mail: info@anbesabank.com
SWIFT Code: LIBSETAA
Address: Haile G.Selassie Avenue, Lex Plaza Building Addis Ababa, Ethiopia