የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት አባላት በሀዋሳ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች ጋር በ2016 የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ዛሬ ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም በሀዋሳ ሳውዝ ስታር ሆቴል አካሄዱ፡፡ በስብሰባው የዘጠኝ ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በሁሉም ቅርንጫፎች አፈጻጸም ላይ የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡
በዚህም በቀሪው የበጀት ዓመት የተያዙ ግቦችን ለማሳካት የሚያግዙ ጠቃሚ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን፤ ቅርንጫፎች በተቀማጭ ገንዘብ አሰባሰብ ፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝት ፣ የገቢ ምንጭን ማሳደግ፣ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ዓይነትና ጥራት እና የሰራተኞችን አቅም በመገንባት ዙሪያ ተወዳዳሪ መሆን እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!