የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣ አንቀጽ 367(1)፣ እና አንቀጽ 370 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀፅ 11(7) መሰረት የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማህበር የባለአክስዮኖች 20ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሠዓት ጀምሮ በስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል። በመሆኑም ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተገኝተው በጉባዔው እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡
- ባንኩን የሚመለከቱ መረጃዎች
- የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መሥርያ ቤት አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ የካ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ የቤት ቁጥር 014፣ የድረ-ገፅ አድራሻ: https://anbesabank.com
- የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡ MT/AA/3/0055690/2015
- የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡ ብር 3,149,681,061.70
- የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡ ብር 3,149,681,061.70
- የ20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- በቀረቡት የስብሰባ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል እና የአክሲዮን ዝውውር ማፅደቅ፣
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የጥቆማ እና የምርጫ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.ኤ.አ በ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደልና አከፋፈል ላይ ውሳኔ መስጠት፣
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያ መወሰን፣
- እ.ኤ.አ የ2024/2025 የሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ወርሃዊ አበል መወሰን፣
- የባንኩ የውጪ ኦዲተር ሹመት ማፅደቅና ክፍያ መወሰን፣እና
- የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፣
ማሳሰቢያ
- በጉባኤው ላይ መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁን ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ ውክልና ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከመካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት 22 ማዞሪያ ሌክስ ፕላዛ ህንፃ ውስጥ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 707 በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅፅ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባኤው ተካፋይ መሆንና ድምጽ መስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
- የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውንና ቅጂ በመያዝ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
- ለምዝገባ ቅልጥፍና ሲባል ባንኩ የባለአክስዮኖችን የመለያ ቁጥር ባስመዘገባችሁት የተንቀሳቃሽ ስልክ መልዕክት የሚላክላችሁ ሲሆን፤ የመለያ ቁጥራችሁን በስብሰባው ዕለት ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!