የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ማኔጅመንት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁሉም ሠራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ማኔጅመንት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለሁሉም ሠራተኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጳጉሜን 4 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ፕሮግራም የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አስፋው ለሁሉም የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች የሰላም፣ የጤናና የስኬት እንዲሆንላቸው በመመኘት በአዲሱ ዓመት ባንኩን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩበት ጊዜ እንደሚሆን ገልፀዋል። ባንኩ ከምንጊዜውም ይበልጥ በርካታ ተስፋ ሰጪ ስራዎች እየሰራ በመሆኑ አሁን ላይ ህብረተሰቡ ለባንኩ ያለው አመለካከት ከሚጠበቀው በላይ አበረታች ስለሆነ ይህን ተስፋ ሰንቀን ረጅም ርቀት መጓዝ እንችላለን ብለዋል።

የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ በበኩላቸው አዲሱ ዓመት ለተጨማሪ ስኬት የሚያበቁን መሠረቶች ጥለን ለውጤት የምንበቃበት እንደሚሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

ማኔጅመንቱና ሰራተኛው በአዲሱ አመት አዲስ ተስፋ ሰንቀው በሁሉም ዘርፍ ጠንክረው በመስራት በበጀት አመቱ የያዝናቸውን አቅዶች በማሳካት ውጤታማነታችንን የምናረጋግጥበት አመት ይሆል ብለዋል።

የዘንድሮው አዲስ አመት ካለፉት ለየት የሚያደርገው ባንኩ አስፀድቆ ወደ ትግበራ ያስገባውን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድ ተፈፃሚ ለማድረግ አንድ ብሎ የጀመረበት በመሆኑ የባንኩ አመራር እና ሠራተኞች እቅዱን ለማሳካት ከመቼውም በላይ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም ለሁሉም የባንኩ አመራሮች እና ባለ ድርሻ አካላት እንዲሁም ደንበኞች መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆንላቸው ምኞታቸውን ገልፀዋል።

Anbesa School Pay

Contact Us

Tel: (+251) 11 662 60 00/60
Fax: (+251) 11 662 59 99
P.O.Box: 27026/1000 Addis Ababa
E-mail: info@anbesabank.com
SWIFT Code: LIBSETAA
Address: Haile G.Selassie Avenue, Lex Plaza Building Addis Ababa, Ethiopia