የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር ኢካገባ/617/17 በተፃፈው ደብዳቤ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1148/2013 መሰረት በባለቤትነት የተያዙ የአክሲዮን ባለቤትነት መዝገቦች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ስር ተቋቋመ ማዕከላዊ የሰነድ ሙዓለ ነዋይዮች ግምጃ ቤት በተዘጋጅ ኤሌክትሮኒክ ዘዴ የሂሳብ መዝገብ ስርዓት ለመተካት እንዲቻል ዝግጁ እንድናደርግ አሳውቆናል፡፡
በመሆኑም የፋይዳ ቁጥረዎን (FAN)፣የአድርሻ ለውጥ አድርገው ከሆን አዲሱን አድራሻ፣ ኢ.ሜል፣ ስልክ ቁጥር፣የቤት ቁጥር፣ ሀገር፣ክልል፣ከተማ፣ ክ/ከተማ፣ወረዳ፣ባለአክሲዮኑ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የድርጅቱ ወኪል ሙሉ መረጃ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ አንበሳ ባንክ ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ በሚገኘው አክሲዮን ክፍል ወይም አቅራቢያችሁ በሚገኝ የአንበሳ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን ቅፅ እንዲሞሉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የስኬትዎ አጋር!