አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ትረስትድ ቴክ ከተሰኘ የቴክኖሎጂ አቅራቢ ደርጅት ጋር በመተባበር የዲያስፖራውን ማህበረሰብ በሀገር ውስጥ በሚከናወኑ ፕሮጀክቶች ላይ ቀጥተኛ የገንዘብ ድጋፍ ተሳትፎ ለማድረግ የሚያስችል ‘Anbesa Fund’ ’የተባለ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ቴክኖሎጂውን በይፋ አስመርቆ ስራ ጀመረ፡፡
ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ተመርቆ ወደ ትግበራ የገባው ‘Anbesa Fund’ የዕርዳታ ማሰባሰቢያ ፕላት ፎርም በሃገራችን በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ችግሮች ሳቢያ የወደሙ ማህበራዊ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እንዲሁም የህብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታት ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ የዲያስፖራውን የገንዘብ ድጋፍ ተሳትፎ የሚጠይቁ ስራዎችን ለማሳለጥ ይረዳል፡፡
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ተከስቶ የነበረውን ጦነት በሠላም መፈታትን ተከትሎ ጦርነቱ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የወደሙ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን የመልሶ ግንባታ ስራዎች ለማከናወን ከዲያስፖራ ማህበረሰብ የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክቶችን ቀርፀው ገንዘብ ለማሳባሰብ ዕቅድና ፍላጎት ያላቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንበሳ ባንክ ያዘጋጀውን አንበሳ ፈንድ (Anbesa Fund platform) ተጠቅመው ገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ለማካናወን አመቺ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸው ይታመናል፡፡
አንበሳ ፈንድ (Anbesa Fund) የእርዳታ ማሰባሰቢያ platform ድረ-ገፅን መሰረት አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሞባይል ስልኮቻችውም ሆነ በሌሎች የትስስር ገፆቻቸው አማካኝነት ወደ አንበሳ ፈንድ ድረ-ገፅ www.anbesafund.com በቀላሉ ገብተው የፈለጉትን ያህል የገንዘብ ልገሳ በማድረግ በሀገራቸው ልማት ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ለመሆን ያስችላቸዋል፡፡
አንበሳ ፈንድ የእርዳታ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕላት ፎርም በአሁኑ ሰዓት ሙሉ የፍተሻ እና የሙከራ ስራው ተጠናቆለት ለትግበራ ዝግጁ የሆነ ሲሆን፤ የተጠቃሚ ደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በኦንላይን የአክስዮን ሽያጭ ማከናወኛ ፕላት ፎርም በማከል ልዩ ልዩ የቢዝነስ ፕሮጀክቶችን ቀርፀው አክስዮኖችን መሸጥ ለሚፈልጉ የስራ ፈጣሪዎችም አመቺ መድረክ ለመፍጠር ይሰራል፡፡ አንበሳ ባንክ በቀጣይ ወደ ተግበራ የሚያስገባው በኦንላይን የአክስዮን መሸጫ ፕላትፎርም በሀገራችን ወደ ትግበራ እየገባ ላላው የStock market የበኩሉን እገዛ እንደሚያደርግም ተስፋ እናደርጋለን፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!