አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ያለ ዋስትና ማስያዣ ለመስጠት የሚያስችለው መተግበሪያ ዛሬ በይፋ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ያለ ዋስትና ማስያዣ ለመስጠት የሚያስችለው መተግበሪያ ዛሬ በይፋ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በደመወዝ ለሚተዳደሩ እና በአነስተኛ የገቢ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያካትት ከምንም ዓይነት የዋስትና ማስያዣ ነፃ የሆነ ዲጂታል የብድር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለው መተግበሪያ ዛሬ በይፋ አስመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ለዚህ የብድር አገልግሎት የሚውል 500 ሚልየን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ መመደቡንም አስታውቋል፡፡

በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ እና መተግበሪያውን ባበለፀገው ሀገር በቀል ድርጅት በሆነው ኳንተም ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሶፎንያስ እምቢበል ዛሬ በሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የተመረቀው አለኝታ የተሰኘ ዲጂታል የብድር አገልግሎት በባንኩ የቁጠባ ሒሳብ ያለው ማንኛውም ደንበኛ ወደ ባንኩ በአካል መቅረብም ሆነ የብድር ዋስትና ማስያዝ ሳያስፈልገው በእጁ ባለው ሞባይል ብቻ በመጠቀም ብድር ማግኘት የሚያስችለው አሰራር ነው፡፡

የአለኝታ ዲጂታል ብድር አቅርቦት መተግበሪያን ያበለፀገው የኳንተም ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሶፎንያስ እምቢበል በበኩላቸው ኩባንያቸው ከአንበሳ ባንክ ጋር በፈጠረው አጋርነት የባንኩን የዲጂታል ብድር አቅርቦት አሰራርን መሰረት በማድረግ ለደንበኞች ቀላልና ምቹ የሆነ መተግበሪያ አዘጋጅቶ ለአገልግሎት ማብቃቱን ገልጸዋል፡፡

ኳንተም ቴክኖሎጂ በዕድሜ ገና ወጣት ቢሆንም ከምስረታው ጀምሮ በኮምፒውተር ሳይንስና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የካበተ ልምድና ክህሎት ባላቸው ባለሙያዎች ስብስብ የተቋቋመ ሲሆን፤ የሀገራችንን E-Payment ስርዓትን ወደ ፊት ሊያራምዱ የሚችሉ ስራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል፡፡

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ

የስኬትዎ አጋር!

https://linktr.ee/anbesabank

Anbesa School Pay

Contact Us

Tel: (+251) 11 662 60 00/60
Fax: (+251) 11 662 59 99
P.O.Box: 27026/1000 Addis Ababa
E-mail: info@anbesabank.com
SWIFT Code: LIBSETAA
Address: Haile G.Selassie Avenue, Lex Plaza Building Addis Ababa, Ethiopia