ባንኩ እና በምሰረታ ላይ ያለው ተጎጋ ስሚንቶ ፋብሪካ ቅዳሜ ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በመቐለ ደስታ ሆቴል የስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነቱን የተፈራረሙት አክስዮን ማህበሩ አጠቃላይ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን በአንበሳ ባንክ ለማድረግ እና ባንኩ ደግሞ ለፋብሪካው ምስረታ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ለማቅረብ ነው።
በዚህም መሠረት የተጎጋ ስሚንቶ ማህበር ከአክስዮን ሽያጭ የሚያሰባስበውን ገንዘብ በባንኩ የሚያስቀምጥ ሲሆን፣ አባላቱም የገንዘብ እንቅስቃሴአቸውን ከአንበሳ ባንክ ጋር እንዲያደርጉ የማግባባት ስራ እንደሚሰራ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አሸናፊ ሃይለ ገልፀዋል።
አንበሳ ባንክ በበኩሉ ፋብሪካው ከምስረታ ጀምሮ እስከ ተከላና ምርት መጀመር ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ የሚያስፈልገውን የፋይናንስ አቅርቦት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን አቶ ዳንኤል ተከስተ የባንኩ ፕሬዝደንት ገልፀዋል።
ለፋብሪካው ግብዓት ከሚያስፈልገው የፋይናንስ አቅርቦት በተጨማሪ የፋበሪካውን አክስዮን በብዛት መግዛት ፈልገው በገንዘብ እጥረት ምክንያት መግዛት ላልቻሉ በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች የአክስዮን ምስክር ወረቀቶቻቸውን በዋስትና በመያዝ ለተጨማሪ አክስዮን መግዣ የሚውል ብድር የሚሰጥ መሆኑን አስታውቀዋል። ከብድር አቅርቦቱ ተጨማሪ አክስዮን የመግዛት ፍላጎት ያላቸው የንግድ ማህበረሰብ አባላትም የሚያካትት መሆኑን ተገልጿል።
በተጨማሪም ባንኩ በቅርቡ ሰራ ላይ ባዋለው አንበሳ ፈንድ በተባለ ዲጂታል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕላትፎርም አማካይነት የፋብሪካውን አክስዮን ሽያጭ ለማቀላጠፍ እንደሚሰራ አቶ ዳንኤል አመልክተዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል