አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከሚያዝያ 12-19 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ “የትግራይ “ህብረት ባዛር እና ኤግዚብሽን” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ባዛር እና ኤግዚብሽን በፕላቲኒየም ደረጃ ስፓንሰር አደረገ።

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከሚያዝያ 12-19 ቀን 2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ “የትግራይ “ህብረት ባዛር እና ኤግዚብሽን” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ባዛር እና ኤግዚብሽን በፕላቲኒየም ደረጃ ስፓንሰር አደረገ።

ላለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታት በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ከሰው ህይወት በዘለለ በኢኮኖሚው ላይ በርካታ ጉዳት ደርሷል፡፡ በተጨማሪም በክልሉ በርካታ አከባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በክልሉ ከፍተኛ የሆነ የሰብል ነክ የአቅርቦት ችግር ተከስቷል። ይህንን ለመቅረፍ  የትግራይ ክልል የህብረት ስራ እና ገበያ ልማት ኤጀንሲ በመቐለ ከተማ ከሚያዝያ 12-19 ቀን 2016 ዓ.ም ለስምንት (8) ቀናት የሚቆይ ሃገር አቀፍ ባዛር እና ኤግዚብሽን በማዘጋጀት ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ዩንዬኖችና የህብረት ስራ ማህበራት እንዲሳተፉ በማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ይህን ፕሮግራም በተሳካ መልኩ ለማከናወን እንዲረዳ በማሰብ የሁል ጊዜ አጋር የሆነው ባንካችን አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር ማድረጉን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።
          አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
                የስኬትዎ አጋር!

Anbesa School Pay

Contact Us

Tel: (+251) 11 662 60 00/60
Fax: (+251) 11 662 59 99
P.O.Box: 27026/1000 Addis Ababa
E-mail: info@anbesabank.com
SWIFT Code: LIBSETAA
Address: Haile G.Selassie Avenue, Lex Plaza Building Addis Ababa, Ethiopia