*Announcement* 21st Ordinary and 7th Extraordinary Shareholders Election Result

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ንስር ማይክሮ ፋይናንስ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረሙ፡፡

በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ሪቴል ባንኪንግ ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሚካኤል ገዛኢ እና በንስር ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ እምባለ በተፈረመው ስምምነት መሰረት ባንኩ የፋይናንስ አካታችነትን ለማስፋት የፋይናንስ ተቋማት ባልተዳረሳባቸው እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የፋይናንስ አቅርቦትን ለማሳለጥ ያለመ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ንስር ማይክሮ ፋይናንስ ለደንበኞቹ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችለው የብድር አቅርቦት ሲያስፈልገው ባንኩ የብድር አቅርቦቱን እንደሚያመቻች ተገልጿል፡፡
                                 
አንበሳ  ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!

Leave A Comment