ባንኩ የ100 ሚልየን ብር ደጋፍ የሰጠው ከትግራይ ልማት ማህበር ጋር ዘላቂ የሆነ አጋርነትና አብሮ የመስራት ስምምነት ትናንት ሰኔ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በመቐለ ፕላኔት ሆቴል በተፈራረሙበት ጊዜ ነው።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ የድጋፍ ገንዘቡን ሲያስረክቡ እንደተናገሩት በጦርነቱ ምክንያት በክልሉ ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና በህብረተሰቡ ስነ- ልቦና ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት ደርሷል። ስለሆነም ህብረተሰቡን ከዚህ ጉዳቱ ፈጥኖ እንዲያገግም ለማድረግ እና ተቋማት መልሰው መገንባትና ለአገልግሎት መብቃት መቻል አለባቸው በማለት ገልፀዋል።
በዚህም መሰረት አንበሳ ባንክ ለመልሶ ግንባታ ሰራዎች ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚቀርብለትን የድጋፍ ጥያቄ በአንድ ጊዜ ምላሽ መስጠት ስለማይችል በትግራይ ልማት ማህበር በኩል ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆኑ ስራዎችን መስራት አማሬጭ አድርጎ ወስዶታል።
አንበሳ ባንክ የሰጠው የ100 ሚልየን ብር ድጋፍ በአምስት አመታት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው።
የትግራይ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተስፋየ ገ/ እግዚአብሔር በበኩላቸው ክልሉን መልሶ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት አንበሳ ባንክ ቀዳሚ በመሆን የአንበሳ ድርሻውን መወጣቱን ገልፀው፤ ከባንኩ ድጋፍ የተገኘው ገንዘብ ለቃላሚኖ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልሶ ግንባታና ስራ ማስጀመሪያ ይውላል ብለዋል።