ትናንት ዓርብ ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ.ም በመቐለ ፕላኔት ሆቴል በተካሄደው የስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓት ላይ የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከሰተ እንደገለፁት ከጮምዓ የብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ጋር አብሮ መስራት ያስፈለገው በስሩ ለሚገኙ ከ90 በላይ አባል የብድርና ቁጠባ ማህበራትና ከ87 ሺህ በላይ አባላቱን ተደራሽ ለመሆን ነው።
ዩኒየኑ የአባል ማህበራቱን አቅም ለማጎልበት በሚያደርገው ጥረት አንበሳ ባንክ የብድርና የፋይናንስ አቅርቦት ለመስጠት እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና በዓቅም ግንባታ ስልጠናዎች አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል።
የጮምዓ ብድርና ቁጠባ ማህበራት ዩኒየን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገ/ ህይወት ኪዳነ በበኩላቸው ዪኒየኑ በስሩ የሚገኙ ከ 87 ሺህ በላይ አባላቱን ከአንበሳ ባንክ ጋር እንዲሰሩ ትስስር ለመፍጠር ያስችለዋል ብለዋል።
ጮምዓ ዩኒየን በአሁኑ ሰዓት ከ90 በላይ ማህበራትና 76,296 አባላት ይዞ በመቐለ ከተማ በመንቀሳቀስ ላይ ሲሆን፤ ከ67 ሚልየን ብር በላይ ካፒታል አለው ::