የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ማኔጅመንት በአዳማ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች ጋር በ2016 የመጀሪያ ሩብ የበጀት ዓመት የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ፡፡
ዛሬ ጥቅምት 03 ቀን 2016 ዓ.ም በአዳማ ናፍሌት ሆቴል በተካሄደ ግምገማ በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ 22 ቅርንጫፎች የዕቅድ ክንውን አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ በአፈጻጸም ላይ በታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ጥልቅ ውይይት ተደርጓል፡፡
ቅርንጫፎቹ በሩብ የበጀት ዓመቱ የታዩ ድክመቶችን በማረምና የነበሩንን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ አሳውቀዋል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!