ለአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለአክስዮኖች የተላለፈ የአክስዮን ሽያጭ ማስታወቂያ
ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው የባለአክስዮኖች 6ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩ ካፒታል ወደ ብር 10 ቢልየን እንዲያድግ መወሰኑ ይታወቃል። ስለሆነም ለሽያጭ እንዲቀርብ ከተፈቀደው ካፒታል ውስጥ ነባር ባለአክስዮኖች ባላቸው የቀደምትነት መብት መሰረት በመጀመሪያ ዙር ለሽያጭ የቀረበውን አክስዮን እንዲገዙ ባላቸው አክስዮን መጠን ድልድል ተደርጓል።
በዚሁ መሰረት የባንኩ ነባር ባለአክስዮኖች የተደለደለላችሁን የአክስዮን ድርሻ ከመጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት በመቅረብ እንድትገዙ ተጋብዛችኋል።
ነገር ግን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የተደለደለላቸውን አክስዮኖች የማይገዙ ባለአክስዮኖች የመግዛት ፍላጎት እንደሌላቸው ተቆጥሮ የባንኩን አክስዮን ለመግዛት ጥያቄ ላቀረቡ ሌሎች ባለአክስዮኖች ወይም አዲስ ገዢዎች የሚሸጥ መሆኑን በማክበር እናስታውቃለን።
አንበሳኢንተርናሽናልባንክአ.ማ
ለበለጠመረጃበስ.ቁ 0116362096/ 0116362065 ወይም 0921613246 ወይም 0972028384 ይደውሉ