በሳፍየር አዲስ ሆቴል ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በዋና መስሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ ሪጅናል ፅ/ቤቶችና ዲስትሪክቶች መካከል ሲካሄድ የቆየው የአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የስራ አመራር ስብሰባ በስኬት ተጠናቀቀ።
በውይይቱ የስድስት ወራት አጠቃላይ ሪፖርት ቀርቦ ሰፋ ባለ መልኩ ግምገማ የተደረገ ሲሆን፤ የግማሽ ዓመቱ ውጤት ጠቅለል ባለመልኩ ሲታይ ብዙ ተሞክሮዎች የተቀሰሙበትና አመርቂ የተባለ የስራ ክንውን የታየበት በጀት ዓመት መሆኑን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ዳንኤል ተከስተ ገልፀዋል። በዚህም በግማሽ ዓመቱ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ዲስትሪክቶች ሰርተፊኬት የተበረከተላቸው ሲሆን፤ በቀሪው የበጀት ዓመት ሁሉም ዲስትሪክቶች ከዚህ በላቀ ውጤት መገኘት እንደሚገባቸው የባንኩ ፕሬዝዳንት አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቀዋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
የስኬትዎ አጋር!

Leave A Comment